Search
Ethiopian
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶሮንቶ እንዲበር የሚያስችል የአየር አገልግሎት ስምምነት ተደረ
አዲስ አበባ, ጥር 15 /2002/ - - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካናዳ ቶሮንቶ እንዲበር የሚያስችል የአየር አገልግሎት ስምምነት ከካናዳ አየር አገልግሎት ጋር ተደረሰ፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ስምምነቱ የተደረሰው ከጥር 4-6 ቀን 2002 ዓ/ም ካናዳ ውስጥ ነው፡፡ ስምምነቱ የተደረሰው በሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄኔራል በኮሌኔል ወሰንየለህ ሁነኛው በተመራ ቡድንና በካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የካናዳ አየር አገልግሎት ዋና ተደራዳሪ ሚስተር ሮበርት ረዱ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ሶስት ጊዜ ወደ ቶሮንቶ እንዲበር የሚያስችል ነው፡፡
በረራው በሁለቱ አገሮች መካከል የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም ግንኙነቶችን በማጠናከር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መግለጫው ጠቁሟል፡፡
በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አየር መንገዱ ወደ ካናዳ እንዲበር ለበርካታ ዓመታት ሲያቀርቡት ለነበረው ጥያቄ ስምምነቱ ምላሽ እንደሰጠም ገልጧል፡፡ (ኢዜአ)
Last Updated (Friday, 22 January 2010 14:53)


